እናት ባንክ አክሲዮን ማህበር ሁለት መኖሪያ ቤት እና አንድ ጂ+3 ጅምር ሆቴል ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

እናት ባንክ አክሲዮን ማህበር ሁለት መኖሪያ ቤት እና አንድ ጂ+3 ጅምር ሆቴል ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Jun 28, 2026)

የድርድር ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- እባ/ንማ/07/2018

እናት ባንክ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ሁለት መኖሪያ ቤት እና አንድ ጂ+3 ጅምር ሆቴል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተስጠው ስልጣን መሰረት ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረቡት ዝርዝር ማብራሪያዎች መሰረት በድርድር ሽያጭ እንዲሳተፉ ይጋብዛል::

ተቁ

የቦታው አገልግሎት

 

ለድርድር የቀረበው ንብረት የሚገኝበት አድራሻ

 

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

የቦታው ስፋት

1

መኖሪያ ቤት

 

አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 10

18/60/64/52/27310/54641/60134/03

 

240.75 ሜትር ካሬ

2

መኖሪያ ቤት +1

 

ኦሮሚያ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ቀበሌ 01

 

447/834/98

200.00 ሜትር ካሬ

 

3

ጅምር ሆቴል +1

 

ኦሮሚያ፣ ሞጆ ከተማ፣ 02 ቀበሌ፣ አፍሪካ ማደያ ፊትለፊት

 

3731/2000

 

1800.00 ሜትር ካሬ

 

ማሳሰቢያ

1. በድርድር ጨረታው የቀረቡትን ንብረቶች ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከማቅረባቸው በፊት ከባንኩ ጋር አስቀድመው ቀጠሮ በመያዝና ማየት ይችላሉ::

2. ገዥዎች የድርድር ጨረታ አካሄድ ዝርዝር መመሪያ የያዘውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ካዛንችስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዥ እና ፋሲሊቲ ሥራ አመራር መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 575 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል መግዛት ይችላሉ::

3. ገዥዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (ሲ.ፒ.ኦ) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

4. ገዥዎች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡት ዋጋ ጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ከሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ ካዛንችስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዥ እና ፋሲሊቲ ሥራ አመራር መምሪያ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሃምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

5. ጨረታው እሮብ ሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ዓ.ም ይዘጋል:: በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል::

6. የድርድር ጨረታው አሸናፊ ሊዝ እና ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈለውን ማናቸውም ክፍያዎች ይከፍላል::

7. የድርድር ጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈብን ዋጋ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መከፈል ይኖርበታል::

8 ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-5585014 ደውለው መጠየቅ ይቻላል::

ማን እንደናት
ማሳሰቢያ፡- በአንድ የጨረታ ሰነድ መጫረት የሚቻለው ለአንድ ንብረት ብቻ ነው::


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *