Addis Zemen (Jun 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሽ ወ/ሮ ፍፁም ይርጉ እና በአፈፃፀም ተከሳሽ አቶ አውግቸው ዘውዴ መካከል ባለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በአፈፃፀም ተከሳሽ አቶ አውግቸው ዘውዴ የትዳር አጋር በሆነችው ወ/ሮ አለምቱ አርጋ ስም በይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር 209/2007 በ300 ካ/ሜ ይዞታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ከልዩ ልዩ ክፍሎች ጋር በስሟ ተመዝግቦ የሚገኝ በጂንካ ከተማ ዐ2 ቀበሌ በሊዝ መንደር የሚገኘ መነሻ ዋጋ ግምት 1,810,160.00 ብር/አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ አስር ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ብር/ የሆነው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒዮ 1/4 በቅድሚያ በማስያዝ እስከ 30/10/2018 ዓ.ም ድረስ መጫረት የሚችሉ መሆኑን የጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዟል፡፡
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት