Addis Zemen (Jun 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አከሲዮን ማህበር ቀጥሎ የተመለከተውን መስፈርት ከሚያሟሉ ተጫራቾች ለጥበቃ እና ጽዳት ሠራተኞች የደንብ ልብስ ሸሚዝ ሱሪ፣ ኮፍያ፣ ካራት፣ የሴት ጓየነ የድርጅቱ አርማ ያለው እና የወንድ እና የሴት ጉርድ ጫማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡–
1ኛ. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድና ሥራ ፈቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ የከፈለበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል።
2ኛ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) የዋጋውን 2% ማስያዝ አለባቸው።
4ኛ. የጨረታ መወዳደሪያ ዝርዝር መግለጫ (Technical) በፖስታ በማሸግ እንዲሁም የፋይናንሻሉን በአንድ ፖስታ በማድረግ እንደዚሁም የሲፒኦ (CPO) በአንድ ፖስታ በማድረግ እና ሁሉንም በአንድ ፖስታ በማጠቃለል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
5ኛ. ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6ኛው ቀን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
6ኛ. በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ሸሚዝ፣ሱሪ፣ ኮፍያ፣ ካራቫት፣ ጫማ እና ጓዮን በራሱ ትራንስፖርት ቡራዮ ከታ ኢትዮ ቴሌኮም ጽ/ቤት ድረስ የአክሲዮን ማህበሩ ቢሮ በማምጣት ያስረክባል፡፡
7ኛ. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሸሚዝ ፣ ሱሪ ፣ ኮፍያ ፣ ካራቫት የወንድም ሆነ የሴት የተለያዩ የጫማ ናሙና ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጫማው መልክና ዓይነት በጥቁር መሆን አለበት፡፡
8ኛ. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል፡፡
9ኛ. ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፡– ፒያሣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ጽ/ቤት የነበረ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ 49 ቢሮ ይሆናል፡፡
Email:- yenget21@gmail.com Tel: 01115578824
የነገ ተስፋ ጥበቃና የጽዳት ሠራተኞች አክሲዮን ማህበር