Reporter (Jun 28, 2026)
የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሣሪያዎች ለመግዛት የወጣ አስቸኳይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ EVANCBEV/02/2026
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association-EVA) በተመረጡ ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚውሉ የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሣሪያዎችን በአስቸኳይ ግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ የተሠማሩ፣ ብታት ያላቸውና ከታች የተቀመጡ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎችና አከፋፋዮች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ማኅበሩ ይጋብዛል :
1. መቅረብ የሚገባቸው ሕጋዊ ማስረጃዎች
1.1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣
1.2.የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (T) ምስክር ወረቀት፣
1.3 በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸው የሚያሳይ የምስክር ወረቀት፣
የጨረታ ሰነድ ግዥ ሂደት
2.1 ፍላጎት ያላቸው እና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 12 (አሥራ ሁለት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማኅበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርቦ ማግኘት ይችላሉ፡፡
2.2 ስነዱን መውሰድ የሚቻለው ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2:30 እስከ 6:30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 እስከ 10:30 ባሉት የሥራ ሰዓታት ውስጥ ነው፦
2.3ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፣ ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ፣ ቼክ ወይም CPO፧አሸናፊ ድርጅት ከተለየ በኋላ ወዲያኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
2.4 ጨረታው በ12ኛው ቀን በ11፡30 ላይ ይዘጋል፣ በ13ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም::
2.5 መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፦
- በስልክ ቁጥር– +251-115-525-020; 091189490209, 0904327608; 0911185503
- አድራሻ፦ ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ ይመናሹ ሕንጻ ፊት ለፊት፡፡
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር