የዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት በቅጥር ግቢው ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የግንባታ ስራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት በቅጥር ግቢው ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የግንባታ ስራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018 

የዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 በጀት ዓመት በቅጥር ግቢው ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የካፈ ስራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት

  1. ደረጃቸው GC6/BC5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የስራ ተቋራጮች 2018 / ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN Number/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽኝ ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2.  አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች የስራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን በመስራት ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
  3.  የሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት/3/ እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ ማወዳደር ኦይችሉም፡፡
  4.  በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሰሪ እና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤት ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የስራ አፈጻጸም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአቸው ወደ ስራ ገብተው ያላስተካከሉ ስራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት /ቴክኒክ/መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና / ኦርጅናል /ሲጠየቁ አርርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid security) 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና Bank Gaurant ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
  7. የስራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ህጋዊ ፍቃዳቸውን እና .. (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት አንስቶ 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ ዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ የስራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የቦታው ሳይት ፕላን በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond security) ፋይናንሻል አንድ ዋና ኦርጅናል እና ሁለት ቅጂ ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ኤቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና ኦድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ11ኛው ከጠዋቱ 4:00 ሰአት አንስቶ 6:00 ሰአት ዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል አንድ ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 600 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 800 ሰአት ላይ ይከፈታል፡፡የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
  10. አሰሪው መስሪያ ቤት የተሻለ ነገር ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡ አሸናፊ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰአት ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ:

አድራሻ በሲዳማ // በዳዬ ከተማ አስተዳደር ዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

ሞባይል ቁጥር፡ 0916812109/ 0913572307

የዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *