Addis Zemen (Jun 28, 2026)
የውሃ ጉድጓድ ጠላቂ ፓምፕ /Electric submersible pump ግዥ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ በ124 ሄክታር ላይ በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን ለእርሻ ልማቱ አገልግሎት የሚውል ሁለት የውሃ ጉድጓድ ጠላቂ ኤሌክትሪክ ሰመር ሰብል ፓምፕ ፣ኤሌክትሪክ ቦርድ ፣ ኬብል እና ተያያዥ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የፓምፑን አጠቃላይ ስፔሲፊኬሽን በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ኩባንያው ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፡፡
3. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
4. የተ.እ.ታ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ቅጹን) የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከኩባያው ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 004 መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በመገኘት የዋጋ ማቅረቢያ ቅጹን መውሰድ ይችላሉ፡፡
8. ጨረታው ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918 481 598 / 0913 696 383 ወይም 058 220 4798 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
10. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
11. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ድረስ በመቅረብ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
12. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
13. ኩባንያው ውሉን እንደየአስፈላጊነቱ በየስድስት ወሩ ሊያድስ ይችላል፡፡
ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ: ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሀይሌ ት/ቤት ጎን፣
ስልክ ቁጥር፡– 058 220 4798፣
አሜል፡ tanaflorapum@gmail.com , tanafloragm@gmail.com ,
ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር