Addis Zemen (Jun 29, 2026)
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨ.ሰ.ቁ፡- NCB-AAMMI-005/2018
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዲስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ለኢንጅነሪንግ ሥራ ለምርት ሥራ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ መካኒካል ማሽኖች እና የሲሲቲቪ ካሜራና ተያያዥ ዕቃዎች አቅርቦት፣ ገጠማና ዝርጋታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት-1፡- የተለያዩ መካኒካል ማሸኖች
- ሎት-2 ፡ የሲሲቲቪ ካሜራና ተያያዥ ዕቃዎች አቅርቦት ገጠማና ዝርጋታ ሥራ
- በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት እቃ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፊቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ክሊራንስ /ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ/ የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል።
(ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣
(ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ የባንክ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፣
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር የስራ ቀን) ቀናት በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሠረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር የሥራ ቀናትን አልፎ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከረፋዱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም።
- ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0221110689/0912264680 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡-አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500ሜ ላይ
ስልክ፡-0221110689/0912264680 ፋክስ፡-0221111866
አዳማ
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ
አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ