Addis Zemen (Jun 30, 2026)
የሀገር ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/19/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሠራተኞች ሰርቪስ አገልገሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018 ዓ/ም)፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት (ገርጂ መንገድ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ህንፃ) ከሚገኘው የፋብሪካ የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሀያ ሺህ) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.PO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም.ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም.ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ 011 442 0216
ፋክስ 011 442 0688
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
አዲስ አበባ