Addis Zemen (Jun 30, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በፌዴራል መንግስት የግዥ አፈጻጸም ሥርዓትን ለመወሰን ባወጣው መመሪያ ቁጥር 1073/17 መሰረት በጋራዥ የመኪና ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- ሎት 1 በጋራዥ የመኪና ጥገና
ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ(ክሊራንስ) ጊዜው ያላለፈበት ከገቢዎች ሚኒስቴር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ህጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ፊት ለፊት የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313 መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሚጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በመሙላት የቴክኒካል እና የፋይናንሽያል ሰነድ በኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313 ማስገባት አለባቸው።
1.ተጫራቾች ለተፈላጊ አቅርቦቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
2. ጨረታው አየር ላይ በዋለበት በ11ኛው ቀን ከሰአት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ከሰአት 8፡30 የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313 ነው። 11ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው ከላይ በተገለጸው ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል።
3. አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ስልክ ቁጥር– 011 123 2696
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር