የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Jun 30, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ትዕግስት ብርሀኔ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሽመልስ አሰፋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት በመ/ቁጥር/310594 በጥር 19 ቀን 2017/ እና በኮ///331461 በሚያዚያ 08 ቀን 2018 / በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 06 ቦሌ አራብሳ ሳይት 5 ብሎክ 996 የቤት ቁጥር 24 2 ፎቅ ባለአንድ መኝታ ቤት የቤቱ ስፋት 65.75/ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,888,143 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺህ አንድ መቶ አርባ ሶስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 30 ቀን 2018 / በሐራጅ ይሸጣል የተጫራቾች ምዝገባ 530 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ//ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም /ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 330 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ//ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ//ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *