የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Jun 29, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ራሔል አለማየሁ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሰለሞን ብሩ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 26/09/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/171271 በ03/04/2018ዓ/ም በ24/03/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር ML/B-14/SN/004 ይዞታው ቤቱ E-ካርታ የሆነ ቤቶ በአቶ ሰለሞን ብሩ አየለ ስም የተመዘገበ የቤቱ ህንጻ ቁጥር 14 የወለል ቁጥር ግራውንድ (Ground) የሆነ የቤቱ ስፋት 45.63ካ/ሜ የጋራ መጠቀሚያ ስፋት 42.08ካ/ሜ ጠቅላላ ስፋት 87 ካ/ሜ የሆነ የቤቱ አገልግሎት የንግድ የሆነ ንግድ ቤቱ ላይ ቀሪ ያልተከፈለ ዕዳ ወለድን ጨምሮ 50% ያልተከፈለ ዕዳ 1,184,388.50( አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ስምንት ከ50/00) ያለበት ሲሆን ቤቱ በአሁኑ ሰዓት ካርታ ያልወጣለት ምክንያቱም  1ኛ የፍ/ባለዕዳ እና 2ኛ ተጠባባቂ የነበሩት ግለሰብ መካከል ባለው ዕግድ ምክንያት ነው በማለት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገልፆልናል፡፡ ስለዚህ የተባለው እግድ የተነሳ ስለሆነ የጨረታ አሸነፊ ለወደፊት ካርታ ሂደት ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን መሃደሩ የሚደራጅለት ይሆናል፡፡ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,824,557 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ አራት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ሰባት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆነ ታውቆ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ 

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን አሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ግቢ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *