የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Jun 29, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ የሊበንወርቅ ላሚሶ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ስዩም ወ/ሰንበት መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/53248 በ16/11/2013 ዓ/ም እና በከመ/ቁ/305507 በግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ/ም በ14/2/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 ክልል ውሰጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 864 የሆነ ቤት የካ/ቁ/35613 በሆነው መኖርያ ቤት ግቢ ውስጥ የተሰሩ 7 ከፍል ቤቶች የ7 ከፍል ቤቶች ያረፈበት 88 ካ/ሜ ከአጠቃላይ ግቢው የቀለበት መንገድ (የሰፈር መንገድ) 34 ካ/ሜ ይነካዋል፡፡ ይዞታው በ1988ዓ.ም በተነሳው አየር ካርታ መሰረት የጋራ ግቢ መሆኑን የሚያሳይ ስለሆነ በጋራ መውጫና መግቢያ ይኖረዋል ተብሎ ታሳቢ የሚደረግ ነገር ግን በአካል ወረዳው ወርዶ ባጣራው መሰረት አሁን ላይ በቤቱ ውስጥ ተከራይ የሚኖሩበትና የሚገቡበትና የሚወጡበት ለብቻ በር ያለው ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 12,13,800 (አስራ ሁለት ሚሊዮን ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *