የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር ለመደበኛ ሥራ አገልግሎት የሚውል ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ አዲስ ተሽከርካሪ (Brand New Fully Electric Vehicle) ከሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር ለመደበኛ ሥራ አገልግሎት የሚውል ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ አዲስ ተሽከርካሪ (Brand New Fully Electric Vehicle) ከሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Reporter (Jun 28, 2026)

የኤሌክትሪክ መኪና ለመግዛት የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ EVA/NCB/EV/01/2026

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association-EVA) ለመደበኛ ሥራ አገልግሎት የሚውል ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ አዲስ ተሽከርካሪ (Brand New Fully Electric Vehicle) ከሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በዘርፉ የተሠማሩ፣ ብቃት ያላቸውና ከታች የተቀመጡ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች ወይም አስመጪዎች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ማኅበሩ ይጋብዛል።

1. መቅረብ የሚገባቸው ሕጋዊ ማስረጃዎች (Eligibility Criteria)

1.1 በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና 2018 . ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ

1.2 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ምስክር ወረቀት፣

1.3 በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸው የሚያሳይ የምስክርነት ወረቀት፣

1.4 ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል የዘመኑ የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) ወረቀት።

1.5 በግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአቅራቢዎች ዝርዝር Federal Procurement Public Agency Web) ውስጥ የተመዘገቡበትን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት፣

2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ

2.1 ፍላጎት ያላቸው እና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.0 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሠላሳ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማኅበሩ /ቤት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርቦ ማግኘት ይችላሉ።

2.2 ሰነዱን መውሰድ የሚቻለው ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2:30 እስከ 6:00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ 7:30 እስከ 10:30 ባሉት የሥራ ሰዓታት ውስጥ ነው

2.3 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ፣ ቼክ ወይም CPO አሸናፊ ድርጅት ከተለየ በኋላ ወዲያኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

2.4 ተጫራቾች የቴክኒክ ሰንደ ኦሪጂናል እና የፋይናንሻል ስነድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ /ቤታችን ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::

2.5 ጨረታው 30ኛው ቀን 1130 ላይ ይዘጋል:: 31ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል:: ሆኖም የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።

2.6 መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦

በስልክ ቁጥር– +251-115-525-020; 091189490209; 0904327608, 0911185503

አድራሻ፦ ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ ይመናሹ ሕንጻ ፊት ለፊት ያገኙናል።

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *