Be'kur (Jun 29, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ አስፋው ታሪክ እና በአፈ/ተከሳሽ ጌትነት ዳኛው መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈ/ተከሳሽ ጌትነት ዳኛው ንብረት የሆነውን በግምጃ ቤት ከተማ 02 ቀበሌ በምሥራቅ አንካሸ ጏጉሳ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ፣በምዕራብ ውዱ ባብል፣ በሰሜን ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው መካከል የሚገኝ የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 2,569,020.5 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሽህ ሃያ ብር ከአምስት ሳንቲም) በማድረግ ጨረታውን ከሰኔ 22/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት በጋዜጣ በማዋል ጨረታው ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም 3፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው ተገኝተው መጫረት ይችላሉ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
አዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት