Addis Zemen (Jul 10, 2026)
የመኪና ጎማና መለዋወጫዎች ግዥ ብሄራዊ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት ለከሚሴ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማ እና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
- ሎት 2 የመኪና ጎማ
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ
- ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ፣ግዥው ከ200,000 በላይ የሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስት /16/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በቀን 20/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ላይ በግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
- ሎት 1. 25,000 ብር /ሃያ አምስት ሺህ ብር
- ሎት 2. 25,000 ብር /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10 % ማስያዝ ይኖርበታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0144 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት