Addis Zemen (Jul 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ወሳሳ ማይከሮ ፋይናንስ አ.ማ. በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በዱከም ክ/ከተማ ላስገነባው B+G+5 ህንፃ የቀሩትን ስራዎች የማስጨረስ እና የጥገና ስራ
በጨረታ ሰነዱ ላይ ዝርዝር ሥራውና መግለጫው በተገለፀው መሠረት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም:
1. ህጋዊ የታደሠ የንግድ ፈቃድ እና የተሰማሩበት ሥራ ፈቃድ።
2. ህጋዊ የምዝገባ ፈቃድ።
3. ህጋዊ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ ስለመሆኑ።
4. ህጋዊ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር።
5. የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ የታደሠ ታክስ ክሊራንስ
6. ደረጃ GC/BC 5 ወይም ከዚያ በላይ ህጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት።
7. ለጨረታ ሲመጡ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺህ/ ብር በወሳሳ ማይከሮ ፋይናንስ ስም የተዘጋጀ CPO ማቅረብ አለበት።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 ብር /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ በወሳሳ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን Technical እና Financial ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 21/11/2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ድረስ በወሳሳ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው 21/11/2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡30 ከሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
12. ወሳሳ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከ ጨ/ከራቡ ወረዳ ልዩ ቦታ ኬንቴሪ ኮንዶሚየም ጀርባ ሶስና ት/ቤት መሄጃ የባቡር ሀዲድን ሳይሻገር ስልክ ቁጥር፡- 011 338 4133/ 09 12 29 23 97
ወሳሳ ማይክሮ ፋይናንስ አ / ማ