በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስና ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ጽ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የመስተንግዶ፣ የህትመት ሥራዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እና የሠራተኛ ካፌ ከነሙሉ እቃው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስና ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ጽ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የመስተንግዶ፣ የህትመት ሥራዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እና የሠራተኛ ካፌ ከነሙሉ እቃው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስና ጽ/ቤት በስሩ ላሎት ጽ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን

  1. የመስተንግዶ
  2. የህትመት ሥራዎች
  3. የትራንስፖርት አገልግሎት
  4. የሠራተኛ ካፌ ከነሙሉ እቃው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

በጨረታው መወዳደር የሚችሉት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በሚያመርቱት ምርት ብቻ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ _ cpo%

  • ሎት. 6233 መስተንግዶ 11,056.00 0.5%
  • ሎት 2. 6213 ህትመት 11,000.00 0.5%
  • ሎት 3. 6232 ትራንስፖርት አገልግሎት 11,000.00 1%
  • ሎት 4 6233 የሠራተኞች ካፌ ከሙሉ እቃዎች ጋር 22,795 0.5%

የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እሸት ት/ቤት ጀርባ የወረዳ 09 አስተዳደር 2ኛፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

1. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ለተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 17/11/2018 11፡30 ሰነድ ማስገባት ይቻላል፡፡ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋ/ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

2. የጨረታ ሳጥን በ11ኛው ቀን 20/11/2018 ጨረታው 3፡30 ታሽጎ በዚያኑ ቀን 4፡00 ተጫራቶች  ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋ/ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ጨረታው ይከፈታል ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

3. ተጫራቾች ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ፍሎድ ያለበት ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

4. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።

5. ተጫራቾች በወሰዱት በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ በመፈረም እና ሕጋዊ ማሕተም በማድረግ ፋይናሻል እና ቴክኔካል ኦርጅናልና ኮፒ በየሎቱ ለየብቻ በማሸግ በወረዳው አድራሻ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10 ቀን 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. በጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ እና ማህተም የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም

7. ተጫራቾች ያለፉበትን እቃዎች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ግምጃ ቤት በራሳቸው ትራንስፖርት ማድረስ አለባቸው።

8. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩበት ዝርዝር እቃዎች መሰረት ናሙናውን አስቀድሞ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታ ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት የለውም።

10. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫት ተጨምሮ መሙላት አለባቸው ይህ ካልሆነ ተቀባይነት የለውም።

11. አነስተኛና ጥቃቅን በሚያመርቱት ምርት ብቻ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ በማያመርቱት ምርት ላይ ግን እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።

አድራሻ፡-

  • በአዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ ወረዳ 9 ኳስ ሜዳ እሽት ት/ቤት ጀርባ ወረዳ 9 አስተዳደር ሕንጻ 2ተኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011-2-30-41-01/011-2-75-90-43

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *