የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት አመታዊ የመኪና መለዋወጫ፣ የመኪና ጎማ፣ በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የመኪና መለዋወጫ እና አመታዊ የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት አመታዊ የመኪና መለዋወጫ፣ የመኪና ጎማ፣ በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የመኪና መለዋወጫ እና አመታዊ የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 11, 2026)

 የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለባቲ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል

  • ምድብ 1፣ አመታዊ የመኪና መለዋወጫ
  • ምድብ2፤የመኪና ጎማ
  • ምድብ3፤ በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የመኪና መለዋወጫ
  •  ምድብ4፤ አመታዊ የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ

የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከሰነዶቻቸውጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2.  የገንዘብ መጠኑ ከ200000 /ሁለት መቶ ሺ/ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል።
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ቅጂዎች ማለትም ኮፒና ኦርጂናል በማለየት በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ባቲ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰየንግድ ፍቃድ ፣የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ለምድብ1፤ለተገለጸው ብር 50,000.00/አምሳ ሺህ ብር/ ለምድብ2፤ ብር 25000.00 ለምድብ3፤ 6000.00 ለምድብ4፤ 3000.00 በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በገቢ መቀቢያ ደረሰኝ በባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋናው ኦሪጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6.  ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበትን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን በባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ዋናና ቅጂ /Orignal and Copy/ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ4/11/2018 ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም እስከ 19/11/2018 ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤትማስገባት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል።
  8.  ግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ጨረታውን በጥቅል ዋጋ /ሎት የሚያወዳድር መሆኑንና ሙሉ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ያልሞላ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑንእናሳውቃለን።
  9. ተጫራቾት በሰነዱ ላይ ስም፣ ማህተምና ፊርማ አሟልተው መገኘት አለባቸው፤ ስርዝ ድልዝ ካለው ከውድድር ውጪ ይሆናል።
  10. የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
  11. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  12. ጽ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለጨረታው የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በባቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስ/ር ቡድን በአካል ቀርበው ወይም በስ.ቁ 0335532123 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ::

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ቦታው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞ ብሄረሰብ

ዞን አስተዳደር የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *