Addis Zemen (Jul 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ገነት ሆቴል የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የበሬና የበግ ተዋጽኦ፣የዶርና የዓሣ ተዋጽኦ እና አትክልትና ፍራፍሬ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
-
- የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- ከዚህ በፊት ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት የነበረው ከሆነ መልካም ሥራ አፈጻጸም ያለው
- ተጫራቾች ስለጨረታው የተሟላ ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከድርጅታችን ፋይናንስ ክፍል ብር 300.00(ሦስት መቶ ብር) መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለገነት ሆቴል በሚል በማሰራት ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ አስተዳደርና የሰው ኃብት ልማት ክፍል በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል። አሥራ አምስተኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ
ለተጨማሪ ማብራሪ ስልክ 0939 50 00 00
ገነት ሆቴል አስተዳደር