Reporter (Jul 19, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የቃሊቲ ሀቢታት ሪል እስቴት የቤት ባለቤትና የነዋሪዎች ኃ/የተ/የህ/ስ ማህበር አድራሻው አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 7 ብሎክ 38 በተለምዶ ቃሊቲ በርታ ሪል እስቴት ግቢ በመባል የሚታወቀው ለሚከተሉት ሥራዎች ተቋራጭ ድርጅት ለመምረጥ የሚያስችል የሥራ ይዘትና የዋጋ ተመን ያለበት የጨረታ ሰነድ እንዲቀርብለት ይፈልጋል::
1. ርዝመቱ ዋና የግቢ ዙሪያ አጥር በአይነቱ የኮንክሪት መደብ ኖሮት ቁመት 2.50 ሜትር በሆነ የብረት ቋሚዎችና ማገሮች የሚሰራ ሆኖ በሜሽ ዋየር የሚሸፍንና ከላይ ላለ ሾክ አደገኛ ሽቦ የሚዘረጋበት ይሆናል::
2. የውስጥ መንገዶች አሁን ያለውን የአስፋልት መንገድ ለመጠገንና ለማጠናከር እንዲሁም ቀሪውን የኮብል ድንግጋይ መንገድ ወደ አስፋልት ደረጃ ለማሳደግ ሲሆን የሚሻሻለው አስፋልት መንገድ ርዝመት 1540 ሜትር ስፋት 7 ሜትር ሲሆን የኮብሉ መንገድ ርዝመት 1944 ሜትር ስፋት 7 ሜትር ይሆናል:: አስፋልቱ ባለ 4 ሴ.ሜ ውፍረት ያለው ኮንክሪት አስፋልት ሆኖ አንድ ወጥ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋል::
ይህንን ስራ ለመስራት ዝግጅቱና ወቅታዊ የሥራ ፈቃድ ያላችሁ ድርጅቶች የዋጋ ተመንና ሥራው ከተጀመረ በኋላ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ጭምር ተገልጾ እንዲቀርብ እናሳስባለን::
ለበለጠ መረጃ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ – አርብ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም 7፡30 – 11፡00
በስልክ ቁጥር፡-0114-71-73-14 መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
የቃሊቲ ሀቢታት ሪል እስቴት የቤት ባለቤቶችና የነዋሪዎች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር