ፀደይ ባንክ የቦታዉ ስፋት 8990 ካ.ሜ. የሆነ የኢንዱስትሪ ሼድ እና ቦታ ለድርጅት አገልግሎት የሚዉል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፀደይ ባንክ የቦታዉ ስፋት 8990 ካ.ሜ. የሆነ የኢንዱስትሪ ሼድ እና ቦታ ለድርጅት አገልግሎት የሚዉል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Jul 19, 2026)

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ ለአቶ ወርቁ ሙኃባዉ ኃይሌ ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በአማራ ክልል ቡልጋ (ቱለፋ) ከተማ የሚገኘዉንና በአቶ አወቀ ዓለሙ ታዬ ስም የተመዘገበዉን የካርታ ቁጥር 704 የቦታዉ ስፋት 8990 ካ.ሜ. የሆነ የኢንዱስትሪ ሽድ እና ቦታ ለድርጅት አገልግሎት የሚዉል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል።

1. የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ተaጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር 42,034,860.14 (አርባ ሁለት ሚሊዮን ሰላሳ አራት ሺኅ ስምንት መቶ ስድሳ ብር ከአስራ አራት ሳንቲም) ብቻ

2. ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጨረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።

4. በጨረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።

5. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ  መክፈልና በጨረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

6. በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።

7. የጨረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል። ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር በራሱ ዉል የሚወስድ ይሆናል።

8. ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።

9. ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላና ፍላጎት ላለዉ ተጫራች በሚሰጠዉ ከፍተኛ ዋጋ ባንኩ እስከ 30% ( ሰላሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።

10. ጨረታዉ የሚካሄደዉ ነሃሴ 14/2018 ከጠዋቱ 3:00—5:00 የተጫራቾች ምዝገባ፤ ከ5:00 እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ጨረታ  በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል።

11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለተጨማሪ መረጃ – ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251 11 558 2978 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *