በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የቧንቧ እና የውሀ መገጣጠሚያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የቧንቧ እና የውሀ መገጣጠሚያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 20, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሴ/መ/ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የቧንቧ እና የውሀ መገጣጠሚያ እቃዎችን በዋን ዋሽ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል::

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::

3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ፡፡

4 የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ከግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮቁጥር4 ማግኘት ይቻላል፡፡

8.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ ለሚወዳደሩበት ለቧንቧና የውሀ መገጣጠሚያ እቃዎች 20,000 ሀያ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና/ኦሪጂናል እና ቅጂኮፒ/ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 28/11/2018ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀላፊ ክፍል በቢሮ ቁጥር1 በቀን 28/11/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

11.ተጫራቹ የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ ስፕስኬሽን በማሟላት ዕቃው የተመረተበትን ሀገር፣ የአምራቹን ስም የዕቃውን ሞዴልና የመሳሰሉትን አካቶ መሙላት ይጠበቅበታል፡፡

12. መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ድምር ዋጋ ወይም በነጠላ ዋጋ የሚያወዳድር መሆኑን ይገልፃል፡፡

13.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 022 472 0080 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

14.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *