በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የቢሮ የጽዳት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የቢሮ የጽዳት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 20, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በመደበኛ በጀት የቢሮ የጽዳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፈኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ የእቃው ግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ኪዲፖ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከመሙላቱ በፊት ቢሮው ድረስ በመምጣት የሚጸዱ ክፍሎችን በአካል ማየት ይኖርባቸዋል፡፡

3. የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባ/ዳር ከተማ የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቁጥር 108 ይከፈታል፡፡

4. በዕለቱ ጨረታው ሲከፈት የተወዳደሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች ብር 12,000 (አስራ ሁለት ሽህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የጽዳት አገልግሎት አይነት አብክመ ገንዘብ ቢሮ ድረስ አገልግሎቱን ማቅረብ (መስጠት) ይኖርባቸዋል፡፡

7. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማረኛ ይሆናል፡፡

8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) መመሪያዎች፣ የውል ቃሎች እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

10. ለበለጠ መረጃ አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 25 82 90 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *