በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 21, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ -02/2019

በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ /ቤት 2019 የበጀት ዓመት በወረዳ ለሚገኙ /ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤
  • ፈርኒቸር፣
  • የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች፤
  • የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና
  • የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፦

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤ እና በፌዴራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ /ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለጽዳት እቃዎች፣ እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ) በዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000073770231 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፤ ንብረት አስተዳደር፣ ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው /ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው 16ኛው የሥራ ቀን ከቀነ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ ለአመቺነት በመረጠው ቦታ ይከፈታል፡ጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የጫረታውን ሂደት አይስተጓጉልም።
  5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ)፤ በአቅራቢያችን በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (CPO.) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ዲክሲስ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳ ገንዘብ /ቤት ድረስ አምጥቶማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  7. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ .ቁጥር 0913349656 0910950695 ይጠይቁ፡፡

በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ /ቤት