Be'kur (Jul 20, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የጐጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሠራተኞች አገልግሎት የሚሰጥ 24 ሰው እና በላይ የሚጭን የህዝብ ሰርቪስ መኪና የሥሪት ዘመኑ 2010 እና ወዲህ የሆነ መኪና ከሚያቀርቡት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት የኮንትራት ውል መከራየት ይፈልጋል፡፡
1. የዘመኑ የታደስ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
3. የተሽከርካሪው ሊብሬ እና ሶስተኛ ወገን የመድን ዋስትና ያላቸው፡፡
4. የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. መኪናው ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ በቀን እስከ 8፡00 በተከራይ ፍላጎት መሠረት መስራት ይጠበቅበታል፡፡
7. ተከራይ የናፍጣ ወጪ ብቻ የሚሸፍን ሲሆን ከናፍጣ ውጭ ያሉትን ወጪዎች በሙሉ አከራይ ይሸፍናል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ቢሮ ቁጥር 19 በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ኢንሹራንስ ያልሆነ ብር 2,000 (ሁለት ሽህ ብር) የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እንዲሁም ቅዳሜ ከቀኑ እስከ 6፡30 ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
11. ጨረታው በ16ኛ ቀን ማለትም ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በጨረታ ኮሚቴዎች ቢሮ ቁጥር 19 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል፡፡
12. አሸናፊው ተጫራች ጨረታውን ማሸነፉ ሲገለጽለት የውል ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ኢንሹራንስ ያልሆነ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
13. ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ የሚፈልጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 891 18 99 /058 891 08 23 በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. አከራይ በሥራ መግቢያና መውጫ ማለትም ጠዋት ከ2፡00 ጀምሮ ቀበሌ 8 ከሚገኘው ከውሃ ጋኑ ተነስቶ በመሃል ከተማ የሚገኙትን ሠራተኞች በመሰብሰብ በ2፡30 ጥገና ጽ/ቤቱ ግቢ ያደርሳል፡፡
የጐጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
ደ/ማርቆስ