ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት አመት ግልጋሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት፣ የቧንቧ፣ የኤሌክትሪክ የወርክ ሾፕ፣ የጽዳት፣ የላብራቶሪ ኬሚካሎችና ባዩሎጂካል እንዲሁም ላብዌር መገልገያ የላብራቶሪ ቋሚ እና የቢሮ የICT ዕቃዎች በሎት በመከፋፈል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት አመት ግልጋሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት፣ የቧንቧ፣ የኤሌክትሪክ የወርክ ሾፕ፣ የጽዳት፣ የላብራቶሪ ኬሚካሎችና ባዩሎጂካል እንዲሁም ላብዌር መገልገያ የላብራቶሪ ቋሚ እና የቢሮ የICT ዕቃዎች በሎት በመከፋፈል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 21, 2026)

የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር NVI 02/2019

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት አመት ግልጋሎት የሚውሉ

  • የተለያዩ የጽሕፈት የቧንቧ፣ የኤሌክትሪክ የወርክ ሾፕ ፤ የጽዳት የላብራቶሪ ኬሚካሎችና ባዩሎጂካል
  • እንዲሁም ላብዌር መገልገያ የላብራቶሪ ቋሚ እና
  • የቢሮ ፤የICT ዕቃዎች በሎት በመከፋፈል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገስፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው የቫት ከፋይ የምስክር ወረቀት ያላቸው ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ሠርተፍኬት፣በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው መጀመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል ከኢንስቲትዩቱ ሒሳብ ክፍል ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10:30 በሥራ ሰዓት ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተያያዘው ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም መሰረት በመሙላት የድርጅታቸውን ማሕተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ ወይም /ቢድ ቦንድ የጠቅላላውን 2% በማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት የሁሉም ሎቶች በተመሳሳይ ሰዓት ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት (አራት ሰዓት) ሲሆን የጨረታ መክፈቻ ሰዓት በተራ ቁጥር አምስት ላይ ወይም በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ይከፈታል።

5. የጨረታ መክፈቻ ሰዓት በተመለከተ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ሎት 1፤2፤ ከ4:30 እስከ 6:00 ሲሆን ሎት 3፤5፤6፤ 7፤8 ከ7:00 እስከ 10፡00 ሰአት ሲሆን ነሐሴ 12 ቀን 2018 ሎት 4፡10 ፤ ከ3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን።

6 ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋም ሆነ በሌላ የጨረታ ጉዳይ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

7. ናሙናን በተመለከተ ለሚያስፈልገው ዕቃ ኢንስቲትየቱ በሚያሳየው ናሙና መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርበታል።

8. አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎቹን ለማቅረብ ውል ከፈረመና ተገቢውን የውል ማስከበሪያ 10% የመልካም ስራ አፈጻፀም ባስያዝ በ15 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ዕቃዎች በሙሉ በናሙናው መሠረት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

9. በጨረታ የወጡ የተለያዩ መገልገያ ፅቃዎች እንዳስፈላጊነቱ 25% ሊቀንሱ ወይም ሊጨምር ይችላል።

10. ንግድ ፍቃድ ቲን ነበር ፤ሲፒኦ የመሳሰሉት ከፋይናንሽያል ሰነድ ተለያይተው ለየብቻ በፖስታ መቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. ቋሚ እቃን በተመለከተ ፋይናሽያልና ቴክኒናል ዶክመንት አንድ ኮፒ እና አንድ ኦሪጅናል ተለያይተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አለፍ ብሎ ከእንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ስማግኘት 09-12-22-98-61 ወይም 09-88-38-83-15 መጠየቅ ይቻላል።
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት