Addis Zemen (Jul 21, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት ለአረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ከሎት 01 እስከ ሎት 140 ድረስ ያሉትን ለማሰራት ስለሚፈልግ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ማህበራት መካከል አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት:-
1. በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ማህበራት፤-
3. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣ በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት።
6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተ ዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር – 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 /ለሃያ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር፤ 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
8. ጨረታ ሰነዱ በስም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል/
9. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
10. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም። ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
11. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ5% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሰንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
13. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከሃያ እስከ ሰላሳ ፐርሠንት (20% እስከ 30%) በታች ከሆነ በተሰበረው ተብለው ተይዞ የሚያልፍ ይሆናል።
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ል/መም/ያ