Addis Zemen (Jul 21, 2026)
የአንደኛ ደረጃ የሐራጅ ማስታወቂያ
የአፈ ከሳሽ…………. አቶ ኃ/ሚካኤል ዮሐንስ
የአፈ/ተከሳሽ……አቶ ግርማ ስዩም
መካከል ስላለው የአፈጻፀም ክርክር ክስ ጉዳይ የማዕ/ጎን/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ምክንያት በጎንደር ከተማ በማራኪ ክፍለ ከተማ በአፈጻፀም ተከሳሽ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቁራሽ መሬት ምዝገባ ቁጥር AM 00205251009 የቦታ ስፋት 200 ካሬ ሜትር G+3 የሆነ በአዋሳኝ፤
- በምስራቅ……. መንገድ…….…….…….በምእራብ……. AM 002052510010
- በሰሜን ……. AM 00205251008….በደቡብ – መንገድ የሚያዋስነው ቤትና ቦታ
በመነሻ ዋጋ 24,333,360.78 ( ሃያ አራት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ብር ከሰባ ስምንት ሳንቲም / በሆነ መነሻ ዋጋ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ የአንደኛ ደረጃ የሐራጅ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማስታወቂያው አየር ላይ ይውላል።
ከላይ በአዋሳኝ የተጠቀሰውን የድርጅት ቤት እና ቦታ መጫረት (መግዛት) የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ሁሉ ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ሰዓት ድረስ ቤቱ ከሚገኝበት ቦታ ድረስ በመቅረብ ቤትና ቦታውን አይቶ መጫረት እና መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንድታሟሉ እንገልጻለን።
- ቤትና ቦታው የድርጅት መሆኑን ተጫራች ማወቅ አለባቸው።
- ጨረታው ከሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአየር ላይ ይውላል።
- ተወዳዳሪዎች ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እሰከ ቀኑ 7፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ቤቱን እና ቦታውን አይቶ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ገዥ ሲያሸንፍ አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ያስይዛል።
- ገዥ ሲያሸንፍ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከከፈለ ስመ–ንብረቱ ወዲያውኑ እንዲዛወርለት ይደረጋል።
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ወቅት መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ የሚወዳደሩ ራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው ይሆናል።
- በጨረታ ወቅት ሁከት የሚፈጥር በህግ ይጠየቃል።ስመ–ንብረት ማዛዎሪያ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል።
- ጨረታው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐራጅ ባይ የሚመራ ይሆናል።
ከዚህ በላይ በዝርዝር የቀረበውን የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ አሟልታችሁ ለመወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ቤቱ ከሚገኝበት ጎንደር ማራኪ ክፍለ ከተማ ቤቱንና ቦታውን በአካል ቀርበው በማየት በጨረታው ቀን እና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት