Addis Zemen (Jul 21, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2019 በጀት አመት ለሴክተር መስሪያቤቶች የሚሆን ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 የጽዳት እቃ
- ሎት 3 የመኪና እቃ
በመሆኑም፡–
- የዘመኑን የታደስ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1 ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ/ ለሎት.2 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ ለሎት3 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ለእያንዳንዱ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን ለየብቻ በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ በታሸጋ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን የስራ ቀን ከልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467710586
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ