የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Jul 20, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ ሙሉእመቤት ጣፋ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወንድወሰን ነጋሽ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት በመ/ቁጥር/10687 23/07/2018 / በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ /ከተማ ወረዳ 04 ብሎክ 1185 የይዞታ ስፋት አጠቃላይ 282 / በዚህ መሰረት በጉለሌ ክፍለ ከተማ LDP ጥናት መሰረት Green Network proposal ውስጥ ያረፈ ሆኖ በሰሜን በኩል 2 /ሜትር Green Area ይነካዋል፡፡ የይዞት መለያ ቁጥር AA0000100401136 የተመዘገበ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 9,004,068 (ዘጠኝ ሚሊዮን አራት ሺህ ስልሳ ስምንት ብር) ሆኖ የትራዛከሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 20 ቀን 2018 / በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 400 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ//ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም /ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 330 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ//ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ` ንግድ ባንከ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ//ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *