የቦታው ስፋት በፕሮፖርሽን 146 ካ/ሜ የመንገድ ጥናት 54 ካ/ሜ የሚነካው የቤቱ ስፋት 75 ካ/ሜ የሆነ የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቦታው ስፋት በፕሮፖርሽን 146 ካ/ሜ የመንገድ ጥናት 54 ካ/ሜ የሚነካው የቤቱ ስፋት 75 ካ/ሜ የሆነ የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Jul 20, 2026)

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለሙበት እነ ወ/ሮ ፍቅርተ ሁንዴ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ በቀለች ሁንዴ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/81634 በ22/8/2007 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/112328 በ28/2/2009 ዓ/ም በ7/09/2009 ዓ/ም በ9/8/2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ክልል ውስጥ የቤት ቁጥር 269 የሆነው ቤት ይዞታው ሰነድ አልባ የጋራ ግቢ የሆነ የቦታው ስፋት በፕሮፖርሽን 146 ካ/ሜ የመንገድ ጥናት 54 ካ/ሜ የሚነካው የቤቱ ስፋት 75 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,373,016 (አምስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰባ ሦስት ሺህ አስራ ስድስት ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል።

ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.112328 በቀን 25/5/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 1,343,254 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ አራት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.PO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *