Addis Zemen (Jul 21, 2026)
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር/ኢኢግልድ-001/2019
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ የኮምፒዉተር፣
- የኔትወርክ፣
- የCCTTV Camera እና ተያያዥ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።
ለዚህ የተዘጋጀዉን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከድርጅቱ ግዢ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶች በተለያዩ በሰም በታሸጉ ፖስታዎች በማሸግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን ከኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።
ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር ብቻ) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡– በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ፒያሳ ከሊፋ ሕንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ (የቀድሞ ጅንአድ) አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2።
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ : በስልክ ቁጥር 011 157-2497 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት