የወልድያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ እና አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና ተ/ጽ/ቤቶች፣ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የመኪና ጎማ እና ባትሪ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ እና አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና ተ/ጽ/ቤቶች፣ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የመኪና ጎማ እና ባትሪ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Jul 20, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ እና አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና ተ/ጽ/ቤቶች፣ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የመኪና ጎማ እና ባትሪ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟማላት ይጠበቅባችኋል።

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑና የምስክር ወረቀት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም እቃ በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ የማጓጓዝ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ ስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በወልድያ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የተጠየቁት የእቃ ዝርዝር መለያ (ሰፔስፊኬሽን) መሰረት መቅረባቸውን በሚረጋገጥ የገዥ መስሪያ ቤት ባለሙያ ሲረጋገጥ እርክክብ የሚፈፀም ይሆናል።

4. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀን ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ስምና ፊርማ፣ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገጹ ማህተም ማድረግ እና መፈረም ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን እንዲሁም ቫት ዊዝሆልድን 7.5 በመቶ ታሳቢ ተደርጎ መሞላት አለበት።

7. ውድድሩ በድምር ዋጋ (ሎት) መሆኑ ታውቆ በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታ ሰነድ የማይመለሰ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።

9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ውሎ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀኑ እሁድ ቅዳሜ ወይም የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የሚከፈት ይሆናል። በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን (የመቀበል) ግዴታ አለባቸው።

10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ ወይም ጥያቄ ካላ ቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለ መምሪያው ማሳወቅ አለባቸው።

11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 40,000 (አርባ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰብ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ ለሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ስለሆነም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል።

13. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ እና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ የተሳሳተ (ስርዝ ድልዝ) የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል በህግም ያስቀጣል።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 7904 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  • ከሎቱ አንድም ሆነ ከአንድ እቃ በላይ ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *