Addis Zemen (Jul 21, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ትዕግስት አሊ እና በፍ/ባለዕዳ አሊ እንድሪስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.118117 በ27/02/2018 ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.120752 በቀን 20/05/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር GE-B02-01-11 ብሎክ 2-11 ገብስ ሜዳ ሳይት የሚገኝ ኮንደሚኒየም ቤት የይዞታ መለያ ቁጥር AA000020600055020111 በአሊ እንድሪስ ስም የተመዘገበ የይዞታ ስፋቱ በተነጻጻሪ 50.11 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ 2,121,016 ( ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ አንድ ሺህ አስራ ስድስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት