የጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 21, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች /የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

.

ሎት

የእቃዉ አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ጊዜ

1

ሎት 1

ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንግ

100,000.00

30-45 ቀናት

2

ሎት 2

የተለያዩ ጎማዎች

100,000.00

30-45 ቀናት

3

ሎት 3

ዘይት እና ቅባት

100,000.00

30 ቀናት

4

ሎት 4

የማሽነሪ መለዋወጫዎች እና ኢንጅን

100,000.00

60 ቀናት

5

ሎት 5

ኤሌክትሮ መካኒካልና አክሰሰሪ አቅርቦት

200,000.00

30-45 ቀናት

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድህረገጽ www.tisisat.com ማግኘት ይችላል፡፡

የተጫራቾች መመሪያ፤

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና TIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመስማራት የተሰጣቸዉን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸዉን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን ከቀኑ 900 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 930 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናዉ /ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድህረገጽ www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተዉን ገንዘብ c.p.o. ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና ቴክኒካል ሰነዳቸዉን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትከክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡

6. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR–03/2017 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

7. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀዉ መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊዉ ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል

8. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 05 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 % የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ የማቅረቢያ ቦታ ባህርዳር ጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች ቢሮ ወይንም መጋዘን ነዉ ፡፡

9. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸዉ መሰረት መሆን አለበት፡፡የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ 90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡

10. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. ማሳሰቢያ፡ ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ሳይሆን በእያንዳንዷ እቃ ነጠላ ዋጋ በሚሞሉት ዋጋ መሰረት ይሆናል፡፡

  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48 26 / 058 320 2548 / በፋክስ ቁጥራችን 058 220 4830 ይጠቀሙ

የጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች /የተ/የግ/ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *