Addis Zemen (Jul 22, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/41/2018
ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥዎች ስፔስፊኬሽን ማውጣት እና የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ የሚያካሂዱ ድርጅቶችን የማዕቀፍ ግዥ ውል በመግባት ለማሰራት ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- Cleaning Machine (Road Sweeper, Spider Lift etc.)
- ሎት 2፡- ICT (Computer, Printer etc.)
- ሎት 3፡- Furniture (Office table, office Chair etc.)
- ሎት 4፡- Construction Work
- ሎት 5፡- Cleaning Materials (liquid soap, Powder soap, Vim etc…)
- ሎት 6፡- Office Equipment (Generator, Water pump etc)
በመሆኑም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-10፡30) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-156 9992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ