Addis Zemen (Jul 25, 2026)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T 625
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአሶሳ፣ሐዋሳ እና ጂንካ ኤርፖርቶች (የአውሮፕላን ማረፊያዎች) የደህንነት አጥር ግንባታ ሥራ የሚያከናውኑ ደረጃ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጮችን እንዲሁም የሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳትፍ ፈቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ጠቅላላ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጭ የሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T625 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለሁሉም ፕሮጀክቶች የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።
የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ሥራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ 180 ተከታታይ ቀናት ይሆናል:: ፕሮጀክቶቹ በአሶሳ፣ ሐዋሳ እና ጂንካ ክልል ኤርፖርቶች ይገኛሉ።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ነሐሴ 15 2018 ዓ.ም ከቀኑ እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: WoldeM@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ