Addis Zemen (Aug 06, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀረሪ ህዝብ ክልል መንግስት የቤቶች ልማት እና የመንግስት ኮንስተራክሽን ኤጀንሲ የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የጨረታ መለያ ቁጥር |
የፕሮጀክት ባለቤት |
የፕሮጀክት ዓይነት |
ለፕሮጀክቱ የሚጠይቀው ደረጃ |
የጨረታ ማሰከበሪያ መጠን |
|
1 |
HHDGCA/W/01/19 የተሻሻለው |
አባድር ወረዳ መስተዳደር ጽ/ቤት |
አባድር ወረዳ መስተዳድር 1B+G+1 ግንባታ ፕሮጀክት |
BC-5/GC-5 & ABOVE |
800,000.00 |
|
2 |
HHDGCA/W/02/19 |
ኤረር ወረዳ መስተዳደር ጽ/ ቤት |
የኤረር ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ግንባታ |
BC-4/GC-4 & ABOVE |
500,000.00 |
|
3 |
HHDGCA/W/03/19 |
ጠቅላይ ፍ/ቤት |
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ህንፃ ግንባታ |
BC-3/GC-3 & ABOVE |
1,500,000.00 |
|
4 |
HHDGCA/W/04/19 |
የአካባቢ ጥበቃና የወንዝ ዳር ልማት ግንባታ ፕሮጀክት |
የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት |
BC-3/GC-3 & ABOVE |
1,500,000.00 |
|
5 |
HHDGCA/W/05/19 |
የጁገል ሆስፒታል እድሳት |
ጤና ቢሮ |
BC-5/GC-5 & ABOVE |
200,000.00 |
1. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና በጨረታ ሰነዱ የተጠየቀውን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሠንጠረዡ በተገለፀው መጠን ሆኖ በሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ የጨረታ የጨረታ ቁጥሩ እና የፕሮጀከቱን ስም የሚገልጽ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ (የጨረታ ቁጥርና የፕሮጀክቱ ስም ያልተገለጸበት ዋስትና ተቀባይነት የለውም።
3. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ፍቃድ ከሚመለከተው አካል ለደረጃው የተሰጠውን ብቃት ማረጋገጫ የግብር፣ ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች በክልሉ ግዥ መመሪያ መሰረት በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ በክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ወይም ከሕጋዊ አካል የተሰጠ አቅራቢነት ፍቃድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከቤቶች ልማት እና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የማይመለስ 5,000 (አምስት ሺህ) ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒውን በመለያየትና ለብቻ በማሸግ እንዲሁም የቴክኒካል መወዳደሪያ ሰነዱን ለብቻ በማሸግ እና ፋይናንስ እና ቴክኒካል ሰነዶችን ሁለቱንም እንደገና በአንድ ፖስታ በማሸግ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በመጻፍ የቤቶች ልማት እና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ቢሮ ቁጥር 15 ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በ22ተኛ ቀን ጠዋት 3፡30 ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ኤጀንሲው የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊልም የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፤– የሐ/ህ/ክ/ መንግስት የቤቶች ልማት እና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
ስልክ ቁጥር፡– 025-666-29-69 ይደውሉ።
የሐ/ህ/ክ/ መንግስት የቤቶች ልማት እና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ