የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የፅዳት አገልግሎት ግብዓት፣ የላውንደሪ ማሽን Air Compressor እና የላውንደሪ ማሽን ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የፅዳት አገልግሎት ግብዓት፣ የላውንደሪ ማሽን Air Compressor እና የላውንደሪ ማሽን ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 08, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/ 2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የተለያዩ ሎቶችን የሚሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

1. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወቀት፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከገቢዎች በጨረታ እንዲሳተፉ የተገለፀበት ደብዳቤ ያላቸው እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ እና በዘርፉ የተሰማሩ የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሰነድ በነፃ ለሚወስዱ ማህበራት በዘርፉ ስለመደራጀታቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩ የእቃ ወይም አገልግሎት አይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል አካውንት ቁጥር 1000014795069 ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በመቀበል ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅቱ ስም ከድርጅቱ አካውንት ተዘጋጅቶ የሚቀርብ

  • ሎት 1፡- የፅዳት አገልግሎት ግብዓት ከተጫራች ሆኖ የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ዓመታዊ ውል
  • ሎት 2፡- የላውንደሪ ማሽን Air Compressor ግዥ የጨረታ ዋስትና ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • ሎት 3፡- የላውንደሪ ማሽን ጥገና ግዥ የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ዓመታዊ ውል በባንክ በተረጋገጠ CPO “ለጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል” ተብሎ በማዘጋጀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ በመሙላት የድርጅታቸውን ማኅተምና ፊርማ አኑረው ፋይናሻል ኮፒ 1 ፣ ቴክኒካል ኮፒ ] ፣ ፋይናሺያል ኦርጅናል 1 እና ቴክኒካል ኦርጅናል 1 በድምሩ 4 ፖስታ በማድረግ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አያግደውም። 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል። 

6. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

7. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ያለምንም አቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት ያለውና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያነት አስይዞ ተገቢውን ውል በመፈጸም እቃዎቹን በሆስፒታሉ ግቢ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት።

8. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር ወይም አቃቂ መሿለኪያ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ 0934 202 236 በስራ ሰዓት ብቻ መደወል ይችላሉ።

የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *