በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) መጠን 41,500 (አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ) ቶን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) መጠን 41,500 (አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ) ቶን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 09, 2026)

ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/24/2018

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) መጠን 41,500 (አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ) ቶን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል። በጨረታ የሚሳተፉ ድርጅቶች በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ወይም አቅራቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃደና የንግድ ምዝገባ ያላቸው፤ አምራች ከሆናችሁ ከክልል መንግሥት የተሰጠ የማዕድን ማምረት ሥራ ፍቃድ ሰርተፍኬት አቅራቢ ከሆኑ የአቅራቢነት ፍቃድ፤ 2018 / የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ምርመራ ውጤት እና ይዞታ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ፤ (አስገዳጅ መስፈርት ሲሆኑ አሟልቶ ያላቀረበ ከጨረታ ይሰረዛል) የተጠቀሱትን ማስረጃዎች (ንግድ ምዝገባ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስና የታክስ ከፋይ ምዝገባ ኮፒ) በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና /ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል መዳረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018 .. ከጠዋቱ 330 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 26 ቀን 2018 .. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *