ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) እና (የዲጂታል ትምህርትን (Digital Education) ለማሻሻል እና ተማሪዎችን እና መምህራንን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚውሉ ግብዓቶችን ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) እና (የዲጂታል ትምህርትን (Digital Education) ለማሻሻል እና ተማሪዎችን እና መምህራንን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚውሉ ግብዓቶችን ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 09, 2026)

የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ግዢ የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ እና ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 16 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ16 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻልየሚል ሙሉ ትኩረቱን በትምህርት ጥራት ላይ ያደረገ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD/ ለእነዚህ አጋር ትምህርት ቤቶች የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) እና (የዲጂታል ትምህርትን (Digital Education) ለማሻሻል እና ተማሪዎችን እና መምህራንን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚውሉ ግብዓቶችን ለመግዛት አቅዷል።

በመሆኑም የሚከተሉትን የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ለማቅረብ የምትፈልጉ እና መስፈርቶቹን የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። የሚገዙት ቁሳቁሶችም የሚከተሉት ናቸው።

ዘርፍ

ዝርዝር መረጃ

ምርመራ

1.

ኮምፒውተር እና ተያያዥ ቁሳቁሶች

ዝርዝር መረጃውን በጨረታው ሰነድ ውስጥ ያገኙታል

 

2.

ወንበር እና ጠረጴዛ

ዝርዝር መረጃውን በጨረታው ሰነድ ውስጥ ያገኙታል

 

ተጫራቾች ማወቅ እና ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡

1. ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በዘርፉ ለመስራት የሚያስችላቸው ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የቲን ሰርተፊኬት እና የቫት ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ የሚጠቀሙ ከሆነ በብርሃንና ሰላም የታተመ የኪው አር ኮድ ያለው ደረሰኝ የሚያቀርቡ፣

4. ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንሰፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶር ማድረስ የሚችሉ፣

5. ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የጽሁፍ ዋስትና መስጠት የሚችሉ፣

6. ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ እና በድርጅታችን ባለሙያ የቴክኒክ ፍተሻ ካለፉ ብቻ የምንቀበል መሆኑ እንዲታወቅ፣

7. የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር CPO በኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰንዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅታችን የጨረታ ሰነዱን በነጻ በመውሰድ ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ቦሌ አለም ህንፃ 7 ፎቅ

ስልክ፦ 0982 882 826

ማሳሰቢያ፦

1. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ግብዓት ከማቅረባቸው በፊት ሳምፕል ማሳየት ይኖርባችኋል።

2. ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርባችኋል። በትክክል ካልተገለጸ ቫት እንደተካተተ ተደረጎ ይቆጠራል።

3. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *