የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 02/2019 የ2019 በጀት ዓመት ለተለያየ አገልግሎት ላይ የሚውሉ መጽሔት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 02/2019 የ2019 በጀት ዓመት ለተለያየ አገልግሎት ላይ የሚውሉ መጽሔት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል


Reporter (Aug 09, 2026)

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 02/2019 2019 በጀት ዓመት ለተለያየ አገልግሎት ላይ የሚውሉ መጽሔት ለማሳተም ከዚህ በታች በተዘረዘረው ዝርዝር መሠረት በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።

  • መጽሄት
  • አጀንዳ
  • ደንብና መመሪያ
  • መጽሀፍ
  • የደረት ቁጥር
  • የተለያዩ መጠን ያላቸው ባነሮች
  • MDF ሰርተፊኬት ሲሆኑ

በዚሁ መሠረት፡

1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤

3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 430 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ እና ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ፡ 0917012504/0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ፋክስ 0116-45-879 – .. 13336

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *