የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 10, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ/ካ/ገ/አስ/ፈ/ቤ/ት 001/2019

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

1.ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት፤ የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በዘመኑ የታደሰ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ (ታከስ ክሊራንስ) ማያያዝ ይኖርበታል፡፡

2. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 2. የፅዳት ዕቃ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 3. የደንብ ልብስ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ፤ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ ሎት 5. ቋሚ የቢሮ እቃ 10,000/ አስር ሺህ/ ሎት 6. የሕትመት አገልግሎት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 7. የመስተንግዶ ግዢ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ስም በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር የውል ማስከበሪያ ላሸነፉበት ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን (10%) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ግን ያስያዙት ሲፒኦ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

4. የጨረታ ሰነድ አቀራረቡ አንድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል አንድ ቴክኒካል ሰነድ ቅጂ፣ እንድ የፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናል አንድ የፋይናንሻል ሰነድ ቅጂ፣ እንዲሁም ሲፒኦ እያንዳንዱ ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ መሆን አለበት፡፡ ፖስታው ላይ ኦርጅናል እና ቅጂ ምልክት በማድረግ እና የድርጅታቸውን
ማህተምና ፊርማ በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ ከኢትዮ ሴራሚክስ ጎን በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል 16ኛ ፎቅ በመምጣት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡30 በተቋሙ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡

6. የጨረታውን ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ በኢ ንግድ ባንክ በኢ/ካ/ገ/አ/ፍ/ቤት በተከፈተ አካውንት (1000670020308) ለእያንዳንዱ ሎት በማስገባት ከፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች ለመወዳደር በመረጡት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በማይቀደድና ጠንካራ መያዣ በማድረግ ለይፋናንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. የሚቀርበው የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡

9. የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የንግድ ፈቃድና የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ በግልጽ የሚታይ ይኖርበታል፡፡

10. አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ንብረት ክፍል ማድረስ

11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አዲራሻ ፡- ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ ከኢትዮ ሴራሚክስ ጎን በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ሕንፃ 16ኛ ፎቅ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት