የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሊፍት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሊፍት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕቃ/02/12/2018

1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሊፍት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ ዕቃ/02/12/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

2. ለኮርፖሬሽኑ ለሊፍት ጥገና አገልግሎት የሚያገለግል የተለያዩ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።

ተቁ

 

የእቃ ዝርዝር

 

የጨረታ ማስከበሪያ

 

1

 

የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ

 

50,000.00

 

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ  በፌዴራል መንግስት ባለቤትነት የተያዙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1070/2017 ሲሆን ከሚፈለገው የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።

4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው የኮርፓሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንክዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ
ዌብሳይት/Website WWW.ash.gov.et  የፖ.ሣ.ቁ. P.0. Box 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *