Addis Zemen (Aug 12, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር ሽካ 001/ 2019
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገ/ት የሚውል የተለያዩ የጽ/መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፤ የጽዳት ዕቃዎችና የቢሮ ውስጥ ቁሳቁሶችን /ፈርኒቸሮችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት :
- ሎት 01 ጽ/መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 02 ጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 03 የቢሮ ውስጥ ቁሳቁስ/ፈርኒቸሮችን/ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
በዚህ መሠረት፡
- በመስኩ ቀጥታ ግንኙነትና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለበት።
- በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት 01 እና 03 ብር 10,000.00 /አስር ሺህ/ ሆኖ ሎት 2 ላይ ለተጠቀሰው ብር 5000.00/አምስት ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግ/ን/አስ/ር ዳይት ቢሮ ገንዘቡን በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መወሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ አገ/ት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል ።
- 16ኛ ቀን የመንግስት ስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት ስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በራሱ ወጪ የዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ በሚገኘው የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ : 047 556 2232 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ