Reporter (Aug 12, 2026)
ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የኮንዶምንየም የንግድ ሱቅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸው የተጠናቀቀ 4 (አራት) ኮንደሚኒየም ሱቆች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች
- የኮንደሚኒየም ሱቆቹ–
1. ቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ሀያት ሳይት ህንፃ ቁጥር 32 የቤት ቁጥር B32/03 የሚገኘውን ስፋቱ 38.80 ካሬ ሜትር የጋር መኖሪያ ኮንደሚኒየም ንግድ ሱቅ
2. በየካ ክፍለ ከተማ የካ ቱሪስት ሳይት ህንፃ ቁጥር B8 የቤት ቁጥር B8/04 የሚገኘወን ስፋቱ 39.87 ካሬ ሜትር የጋር መኖሪያ ኮንደሚኒየም ንግድ ሱቅ
3. ጎፋ መብራት ሀይል ሳይት የሚገኘውን ህንፃ ቁጥር B91 የሚገኘውን ስፋቱ 36.77 ካሬ ሜትር የቤት ቁጥር B91/02 የጋራ መኖሪያ ኮንደሚኒየም ንግድ ሱቅ
4. ን/ስ/ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ ሳይት የሚገኘውን ህንፃ ቁጥር B2 ስፋቱ 39.17 ካሬ ሜትር የቤት ቁጥር 2/04 የጋራ መኖሪያ ኮንደሚኒየም ንግድ ሱቅ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታ ስዓት ድረስ የንግድ ሱቆቹ በሚገኙበት ሳይት ማየት ይቻላል።
- የጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ/ ለኮንደሚኒየም ሱቆች ከተ.እ.ታ በፊት የሚገዛበትን ዋጋ 10% ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲፒኦ ገቢ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎኘ ከጨረታ መዝጊያ ስዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው ነሀሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ጊቢ ውስጥ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው ወይም 8868 መጠየቅ ይችላሉ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት