በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 13, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/…/ 2019 ዓ.ም

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶች ማለትም

  • ሎት አንድ የደንብ ልብስ ፤
  • ሎት ሁለት አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
  • ሎት 3፡-የጽዳት እቃዎች ፣
  • ሎት አራት የመኪና ጎማ፤
  • ሎት አምስት የህትመት አገልግሎት እና
  • ሎት ስድስት፡ የትራንስፖርት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ከ (egp / www.ppa.gov.et  ) ማቅረብ የሚችሉ፤ እንዲሁም ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች እና አገልግሎቶች ማለትም ለሎት 1 (የደንብ ልብስ) ብር 50,000.፤ ለሎት 2 (አላቂ የቢሮ እቃዎች) ብር 30,000፤ ለሎት 3 (የጽዳት እቃዎች) ብር 25,000,፤ ለሎት 4 (የመኪና ጎማ) ብር 7,000፤ ለሎት 5 እና 6 ለእያንዳንዳቸው በተናጥል የ5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዥያ ትእዛዝ CPO ብቻ (አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ) በሚል አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 % ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ከለይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት (10) አስር ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

5. ከጥቃቅንና አነስተኛ / የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ ተጫራቾች ከሆኑ እሴት ጨምረው የሚያመርቱት ምርት ምን እንደሆነ በጽሁፍ የብቃት ማረጋገጫ ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል። የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ / ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው እንዲሁም

6. የጨረታ እና የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር የሚችሉ ይሆናል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ/ወረዳ 7 አስተዳደር ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡-ቃሊቲ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር: 011-471-7931

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ ቤት