Addis Zemen (Aug 13, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ራሔል አለማየሁ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሰለሞን ብሩ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 164150 26/09/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/171271 በ03/04/2018ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/171271 በ24/03/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር MLB- 14/SN/004 ይዞታው ቤቱ E-ካርታ የሆነ ቤቶ በአቶ ሰለሞን ብሩ አየለ ስም የተመዘገበ የቤቱ ህንጻ ቁጥር 14 የወለል ቁጥር ግራውንድ (Ground) የሆነ የቤቱ ስፋት 45.63 ካ/ሜ የጋራ መጠቀሚያ ስፋት 42.08 ካ/ሜ ጠቅላላ ስፋት 87 ኪሜ የሆነ የቤቱ አገልግሎት የንግድ የሆነ ንግድ ቤቱ ላይ ቀሪ ያልተከፈለ ዕዳ ወለድን ጨምሮ 50% ያልተከፈለ ዕዳ 1,184,388.50( አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ስምንት ከ50/100) ያለበት ሲሆን ቤቱ በአሁኑ ሰዓት ካርታ ያልወጣለት ምክንያቱም 1ኛ የፍ ባለዕዳ እና 2ኛ ተጠባባቂ የነበሩት ግለሰብ መካከል ባለው ዕግድ ምክንያት ነው በማለት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገልፆልናል። ስለዚህ የተባለው እግድ የተነሳ ስለሆነ የጨረታ አሸናፊ ለወደፊት ካርታ ሂደት ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን መሃደሩ የሚደራጅለት ይሆናል፤ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,824,557 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ አራት ሸህ አምስት መቶ ሃምሳ ሰባት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 8 በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፤ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት