በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 15, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 001/2019

በአዲስ ከተማ /ከተማ ጤና /ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር ጤና ጣቢያ 13 (በአስራ ሶስት) ሎት ማለትም፤

  • በሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ፤
  • ሎት 3 የጽዳት ዕቃ ግዥ
  • ሎት 4 የጥገና የህንጻ መሳሪያዎች ዕቃ ግዥ
  • በሎት 5 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ
  • በሎት 6 የደንብ ልብስ ስፌት ስራ
  • በሎት 7 ፈርኒቸር ዕቃዎች ግዢ
  • በሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ፤የሊፍት እና የጄኔረተር ጥገና፤
  • በሎት 9.የተለያዩ ህትመቶች
  • በሎት 10 የመኪና ኪራይ፤
  • በሎት 11 መድሃኒትና ሪኤጄንት ግዥ፤
  • በሎት 12 የህጻናት ማቆያ የፓርቲሽን ስራ እና
  • በሎት 13 የላውንደሪ፤ የእጅ መታጠቢያ ገንዳ እና የቆሻሻ ማቃጠያ ግንባታ በብሎኬት በውል የሚቆይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

ሎት 1

ሎት 2

ሎት3

ሎት 4

ሎት 5

ሎት 6

ሎት 7

ሎት 8

ሎት 9

ሎት 10

ሎት11

ሎት 12

ሎት 13

10,000

15,000

7500

2000

40,000

5,000

10,000

4000

14,940

2000

80,000

75,000

6000

 

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ግብር ከፋይነት ምዝገባ(TIN) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበና ሰርተፊኬት ያለው ፤አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ (በዌብ ሳይት) ተመዝጋቢ የሆነ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ለመድሃኒት አቅራቢዎች ከኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው፤ ለግንባታ ፈቃድ ከአዲስ አበባ ግንባታና ፈቃድ ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ያለው፤ እንዲሁም 2019 . በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል (ከገቢዎች) በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚሰጥ የታደሰ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ፡ለእንዳንዱ ሎት ከአጠቃላይ ለበጀት አመቱ ከተበጀተው በጀት 0.5 እስከ 2% የተሰላ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ ሎት ለብቻው በባንክ በተረጋገጠ CPO በአዲስ ከተማ /ከተማ ጤና /ቤት አስኮ አዲስ ሰፈር ጤና ጣቢያ ስም የተሰራ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  3. የድጋፍ ደብዳቤ ለጨረታ ማስከበሪያ የተጻፈ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ብቻ ነው፤ ሰነድ በነጻ እንዲወስዱ ተብሎ ከተጻፈ ለሰነድ መውሰጃ ብቻ ነው የሚገለግለው።
  4. የድጋፍ ደብዳቤ ካደረጀው አካል የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ ይዞ ሲመጡ ሰነዱን በነጻ ይወስዳሉ፤አምራቾች (በጥቃቅንና አንስተኛ ለተደራጁ ማህበራት) ማኑፋክቸርንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ በሚያመርቱት ምርት ላይ 3% አስተያየት ይደረግላቸዋል።
  5. የሚታዘዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ተቀባይነት የሚኖረው የሲፒኦ ቁጥር በግልጽ የሚታይ ከሆነ፤የተጫራቹ ስም በግልጽ የሚነበብ ከሆነ ሲፒኦ ጀርባ ላይ የባንኩ ማረጋገጫ ማህተም ያለው ከሆነ ብቻ ነው ተቀባይነት የሚኖረው።
  6. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት 400 ብር /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአዲስ ከተማ /ከተማ ወረዳ 14 የአስኮ አዲስ ሰፈር ጤና ጣቢያ 5 ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  7. በክፍል 6 ላይ በቴክኒክ መመዘኛዎች ላይ ተሞልቶ፤ተፈርሞ እና ማህትም ተደርጎ በሁሉም ገጽ ላይ ተፈርሞበት የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ ሙሉ የጨረታ ሰነድ (መመሪያው) ተመላሽ ይደረጋል።
  8. ተጫራቾች ከአንድ ሎት በላይ የተወዳደሩ ተወዳዳሪዎች እያንዳንዱን ሎት ለየብቻው ቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ አንድ (1) ኮፒ አንድ (1)፤ፋይናንሺያል ኦርጂናል ሰነድ አንድ (1) ኮፒ አንድ (1) ብሎ በየሎቱ ለየብቻው በሰም በማሸግ በጉልህ በሚታይ በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ኦርጅናል አንድ (1) ኮፒ አንድ (1) ፤ፋይናንሺያል ኦርጂናል ሰነድ አንድ (1) ኮፒ አንድ (1) በድምሩ አራት (4) ፖስታ በአንድ ታሽጎ በጉልህ በሚታይ በመጻፍና የድርጅቱን ማህተም በማድረግና በመፈረም በታሽገ ፖስታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን እስከ 1130 የጨረታ ሰነድ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአዲስ ከተማ /ከተማ በጤና /ቤት በወረዳ 14 የአስኮ አዲስ ሰፈር ጤና ጣቢያ የግዢ ቡድን 5 ፎቅ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ በ11ኛው ቀን ከረፈዱ 300 ታሽጎ ከረፋዱ 330 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡10ኛው ቀን ከተጠናቀቀ በኃላ በ11ኛው ቀን የመጫረቻ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አይፈቀድም።
  10. መስሪያ ቤቱ ወይም ጤና ጣቢው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የጨረታ ዋጋ ሲገባ ከነቫት መሆን ይኖርበታል።

አድራሻ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከቅዱስ ክሊንክ ወረድ ብሎ / ህንፃ 5 ፎቅ የአዲስ ከተማ /ከተማ በጤና /ቤት ወረዳ 14 የአስኮ አዲስ ሰፈር ጤና ጣቢያ 20/80 ኮንዶሚኒየም  ጀርባ ያገኙናል።

ስልክ ቁጥር 0112-79-97-56

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር ጤና ጣቢያ