Addis Zemen (Aug 18, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ህትመቶች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- ቋሚ የቢሮ ውስጥ ፈርኒቸሮች፣
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ኮምፒዉተሮች፤
- ጄኔተሮች፣
- የግንባታ ዕቃዎች፣
- የሥልጠና ዕቃዎች እና የሠራተኞች የደንብ ልብስ
የመሳስሉትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የዕቃ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፤
- ተጫራቾች በአነስተኛ ቀን የተደራጁ ከሆነ በአደራጃቸው ወኪል በዘመኑ የተሰጠ የጽሑፍ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ስለጨረታው መሉ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዕቃዎቹን እስፔሲፊኬሽን የማይመለስ ብር 100 (መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአብቹና ፕኣ ወረዳ ፍ/ቤት በመምጣት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒውን በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 3 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 08 መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አሥር ሺህ) በባንክ የተመሰከረ CPO ማቅረብ የሚችል።
- ጨረታው የሚከፈተው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው የሥራ ቀን ሆኖ በዚሁ ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ7፡40 ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ ቅዳሜና እሑድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ7፡40 በወረዳ ፍ/ቤት ይከፈታል።
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን አብቹና ፕኣ ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስገባት አለበት።
- የተጠየቁትን ዕቃዎች ሠርዘው ወይም ደልዘው መጻፍ ክልክል ነው።
- የዕቃውን ኮድ ወይም አይነት ለመተው ከፈለጉ ከታች ማሳሰቢያ ብለው በመፃፍ ይፈርሙበት
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የተጠየቁት ዕቃዎች በመሉ ደረጃቸውን የጠበቁና ኦርጂናል መሆን አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 12 66 51 57/ 011 621 0053/24
ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ፕኣ ወረዳ ፍ/ቤት